Article text
፩/ ማንኛውም ነጋዳ ወይም የንግድ ማህበር በንግድ
መዝገብ የሚመዘገበው የንግድ ሥራው ዋና
መሥሪያ ቤት ባለበት ስፍራ ሥልጣን በተሰጠው
መዝጋቢ አካል ነው፤ የንግድ ሥራውን ዋና
መሥሪያ ቤት አድራሻ የመምረጥ መብት የነጋዳው
ነው።
፪/ በሕግ በተለየ ሁኔታ ካልተወሰነ በስተቀር የንግድ
ሥራው ዋና መሥሪያ ቤት በውጭ አገር የሆነ
ነጋዳ ወይም የንግድ ማህበር የንግደ ቅርንጫፍ
፶፫
54 ____________________________________________________ የንግድሕግ
ወይም ወኪል መሥሪያ ቤት ባለበት ስፍራ
ሥልጣን በተሰጠው መዝጋቢ አካል ይመዘገባል።