Article text
፩/ ፇቃደኛ ከሆኑ በባለአክሲዮንነትም ሆነ በወኪልነት
ስም በጉባዔው ስብሰባ ላይ ከተገኙት ውስጥ ከፍተኛ
ድርሻ ባላቸው አባላት መካከል በሚደረግ በስምምነት
የተወሰኑት ባለአክሲዮኖች ድምፅ ቆጣሪ ይሆናለ።
፪/ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፩) መሰረት የድምፅ
ቆጣሪ መሆን የሚችለት ባለአክሲዮኖች ፇቃደኛ
ካልሆኑ ወይም በጉባዔው የተገኙት ባለአክሲዮኖች
ላላ ሰው መምረጥ ከፇለጉ ስብሰባው እንደተጀመረ
የድምፅ ቆጠራውን ለማድረግ የሚያስፇልጉ ድምፅ
ቆጣሪዎችን መምረጥ አለባቸው።
፫/ በዚህ አንቀፅ ንዐስ አንቀፅ
(፩) እና
(፪) የተደነገገው
ቢኖርም በኤላክትሮኒክ ዘዳ የሚደረግ ስብሰባን
ድምፅ ለመቁጠር አስተማማኝ የሆነ የድምፅ ቆጠራን
ለማድረግ የሚያስችል ቴክኖልጂን መጠቀም
ይቻላል።