Article text
፩/ የአስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ውሳኔ የጸና የሚሆነው
በጉባዔው የተገኙት ድምፅ የመስጠት መብት
፪፻፺፩
292 ____________________________________________________ የንግድሕግ
ያላቸው አክሲዮኖች ከወከለት ካፒታል ሁለት
ሦስተኛውን በሚወክለት ድምፅ ከተደገፇ ነው፤
ለድምፅ ብልጫው አቆጣጠር ስላት ድምፅ
ያልሰጡም ሆነ ድምፅ ያልተጻፇባቸው የድምፅ
መስጫ ወረቀቶች ግምት ውስጥ አይገቡም።
፪/ አስቸኳይ ጉባዔው የማህበሩን ዜግነት መለወጥ
የሚችለው ድምፅ የመስጠት መብት ያላቸውን
ባለአክሲዮኖች ሙለ ድጋፍ ያገኘ እንደሆነ ነው።
፫/ አስቸኳይ ጉባዔው አንድ ባለአክሲዮን ከፇቃደ ውጪ
በማህበሩ ውስጥ ተጨማሪ መዋዕለ ንዋይ
እንዱያፇስ መወሰን አይችልም፤ በመሆኑም
ተጨማሪው ገንዘብ ከማህበሩ መጠባበቂያ ገንዘብ
ወይም ሉከፊፇል ከሚችል ትርፍ የሚከፇል ካልሆነ
በስተቀር፤ በነባር አክሲዮኖች ላይ የተጻፇውን ዋጋ
በመጨመር የማህበሩን ዋና ገንዘብ ማሳደግ
የሚቻለው የባለአክሲዮኖች ሙለ ድጋፍ የተገኘ
እንደሆነ ነው።
፬/ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፪) እና
(፫) የተመለከቱት ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው
ምልዓተ ጉባዔው ተሟልቷል የሚባለው
በሚከተለት ሁኔታዎች ነው ፡፪፻፺፪
፫
293 ____________________________________________________ የንግድሕግ
ሀ) በመጀመሪያው ጥሪ ድምፅ የመስጠት መብት
ካላቸው አክሲዮኖች ውስጥ ቢያንስ የማህበሩን
ዋና ገንዘብ አንድ ሦስተኛ የሚወክለ
ባለአክሲዮኖች ወይም ወኪልቻቸው የተገኙ
እንደሆነ፤
ለ) በሁለተኛው ጥሪ ድምፅ የመስጠት መብት
ካላቸው አክሲዮኖች ውስጥ ቢያንስ የማህበሩን
ዋና ገንዘብ አንድ አራተኛ የሚወክለ
ባለአክሲዮኖች ወይም ወኪልቻቸው የተገኙ
እንደሆነ፤
ሐ) በሦስተኛው ጥሪ ድምፅ የመስጠት መብት
ያላቸው አክሲዮኖች የሚወክለት ዋና ገንዘብ
(ካፒታል) ግምት ውስጥ ሳይገባ ባለ
አክሲዮኖች ወይም ወኪልቻቸው የተገኙ
እንደሆነ፤ ነው።