Article text
ስለ አባል ኃላፉነት ውስንነት በዚህ ሕግ አንቀጽ ፭፻፴፬
ንዐስ አንቀጽ
(፫) የተደነገገው ቢኖርም፤ ማንኛውም ባለ
አንድ አባል ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር አባል
ወይም ማህበሩ ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ቁጥጥር
ያለው ላላ ሰው ከዚህ በታች ከተመለከቱት አንደን
፫፻፺፬
395 ____________________________________________________ የንግድሕግ
ፇፅሞ ከተገኘ ከማህበሩ ጋር በአንድነት እና በተናጠል
ተጠያቂ ይሆናል፦
፩/ ማህበሩን፣ ወይም የማህበሩን ገንዘብ ጠያቂዎች
ጉዲት ላይ የሚጥል ሕገ-ወጥ ድርጊት ሆን ብል
ከፇፀመ፤
፪/ የባለ አንድ አባል ማህበር ንብረትን ከራሱ ንብረት
ጋር ከቀላቀለ፤
፫/ የባለ አንድ አባል ማህበርን እና የራሱን ማንነት
ካልነጣጠለ፤
፬/ ስለማህበሩ የፊይናንስ አቋም የማህበሩን ገንዘብ
ጠያቂዎች ሉያሳስት የሚችል መረጃ ሆን ብል
ካወጣ፤
፭/ ያለ ተመጣጣኝ ክፍያ የማህበሩን ሀብት ለራሱ
ወይም ለሦስተኛ ወገኞች የግል ጥቅም ካዋለ፤
፮/ በሕግ ሉከፇል ከሚችለው በላይ የትርፍ ክፍያ
ከፇጸመ፤ ወይም
፯/ ላልች ተመሳሳይ ተግባራትን ከፇጸመ።