Article text
፩/ መልሶ የማደራጀት ኃላፉው በባለዕዲው ተዘጋጅቶ
በገንዘብ ጠያቂዎች የተሻሻለውን መልሶ የማደራጀት
ዕቅድ እንዱሁም አግባብነት ያለው በገንዘብ
ጠያቂዎች የተዘጋጀ ማንኛውንም የአጸፊ ሀሳብ
፭፻፵፯
548 ____________________________________________________ የንግድሕግ
አደራጅቶ እያንዲንደ የገንዘብ ጠያቂዎች መደብ
ድምፅ እንዱሰጥበት ያቀርባል።
፪/ በእያንዲንደ የገንዘብ ጠያቂዎች መደብ ውስጥ ካለው
አጠቃላይ የክፍያ ጥያቄ ውስጥ ሁለት ሦስተኛው
ያላቸው አንድ ወይም ከዚያ በላይ ገንዘብ ጠያቂዎች
መልሶ የማደራጀት ዕቅደ እንዱጸድቅ በጽሁፍ
በሚደረግ ስምምነት አማካኝነት ጭምር ድምፅ
ሲሰጡ መልሶ የማደራጀት ዕቅደ ተቀባይነት
ያገኛል፤ ማሳወቂያ ተሰጥቷቸው በስብሰባው ላይ
በአካልም ሆነ በሕጋዊ ወኪላቸው አማካኝነት
ያልተገኙ ገንዘብ ጠያቂዎች ድምፅ በመስጠት ረገድ
ከግምት ውስጥ አይካተቱም።
፫/ በእያንዲንደ የገንዘብ ጠያቂዎች መደብ ስብሰባ ላይ
ሁለት ሦስተኛ አብላጫ ድምፅ ያላገኘ እንደ ሆነ፤
መልሶ የማደራጀት ዕቅደ በባለዕዲው እና
በአብዛኛዎቹ የሚመለከታቸው ገንዘብ ጠያቂዎች
መደቦች ከጸደቀ ተቀባይነት ያገኛል።
፬/ በዚህ አንቀጽ በንዐስ አንቀጽ
(፪) የተመለከተው
አብላጫ ድምፅ ያልተገኘ እንደሆነ ከአክሲዮን
፭፻፵፰
549 ____________________________________________________ የንግድሕግ
ባለቤቶች መደብ ወይም ንብረት በሚጣራበት ሁኔታ
ውስጥ የባለዕዲው ሀብት በሚገመትበት ጊዜ ምንም
ክፍያ ከማያገኝ ወይም ምንም ጥቅም ከማይኖረው
ላላ ማንኛውም መደብ ውጭ የሆነ ቢያንስ አንድ
የገንዘብ ጠያቂዎች መደብ ዕቅደን በመደገፍ ድምፅ
ከሰጠ ዕቅደ እንደጸደቀ ይቆጠራል።
፭/ በስብሰባው ላይ ባይገኙም እንኳን ለገንዘብ
ጠያቂዎች ተጨማሪ ማሳወቂያ ሳይሰጥ የገንዘብ
ጠያቂዎች መደቦች ስብሰባዎች ወደ ቀጣዩ የሥራ ቀን
ሉተላለፈ ይችላለ።