Article text
፩/ ሥራ አስኪያጁ የማህበሩን ዓላማ ለማሳካት
በማህበሩ ስም ማንኛውንም ሕጋዊ ተግባር
ያከናውናል።
፪/ የሥራ አስኪያጁን ሥልጣን የሚገድቡ ስምምነቶች
ሦስተኛ ወገኖችን መቃወሚያ የሚሆኑት በንግድ
መዝገብ የተመዘገቡ ወይም ሦስተኛ ወገኖች
የሥራ ኃላፉነቱን የሚያዉቁ መሆናቸው
የተረጋገጠ እንደሆነ ነው።
፫/ የማህበሩ ቆይታ ከአንድ ዓመት በላይ ሲሆን ሥራ
አስኪያጁ በየዓመቱ መጨረሻ የማህበሩን የሥራ
ክንውን ሪፖርት አዘጋጅቶ ለሸሪኮች ማቅረብ
አለበት።