Article text
ስለመጥራት
፪፻፵፯
248 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፩/ ሕግ ወይም የማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ
በሚጠይቀው መሰረት የዲይሬክተሮች ቦርድ ወይም
ተቆጣጣሪ ቦርድ ጠቅላላ ጉባዔው እንዱሰበሰብ ጥሪ
ሳያደርጉ የቀሩ እንደሆነ፣ ጥሪውን ኦዱተሮቹ
ማድረግ አለባቸው።
፪/ ከማህበሩ ዋና ገንዘብ ውስጥ ቢያንስ አስር በመቶ
ድርሻ ባላቸው ባለአክሲዮኖች ጥያቄ የቀረበላቸው
እንደሆነ፤ ኦዱተሮች ጠቅላላ ጉባዔ እንዱሰበሰብ ጥሪ
ማድረግ አለባቸው።
፫/ ኦዱተሮች ከአንድ በላይ ከሆኑ በማህበሩ መመስረቻ
ጽሁፍ በተመለከተው መሰረት በጋራ ጠቅላላ ጉባዔ
እንዱሰበሰብ ጥሪ ማድረግ ይችላለ፤ አስፇላጊ መስል
ሲታያቸው ስብሰባው ከማህበሩ ዋና መሥሪያ ቤት
ወይም በማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ ከተጠቀሰው
ቦታ ውጭ እንዱደረግ መወሰን ይችላለ።
፬/ በዚህ አንቀጽ ድንጋጌ መሰረት ኦዱተሮች ስብሰባ
የጠሩ እንደሆነ የዕለቱን ስብሰባ አጀንዲ ያዘጋጃለ፤
ስብሰባውን መጥራት ስለአስፇለገበት ምክንያትም
ለጠቅላላ ጉባዔው በጽሁፍ ሪፖርት ያቀርባለ፤
ከኦዱተሮቹ አንደ ጉባዔውን በሰብሳቢነት ይመራል።
፪፻፵፰
249 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፭/ ጠቅላላ ጉባዔውን በመጥራት ወይም ባለመጥራት
ላይ ኦዱተሮቹ ያልተስማሙ እንደሆነ፣ ከኦዱተሮቹ
አንደ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፫) እና
(፬) የተመለከተውን ሥልጣን ተግባራዊ ለማድረግ
የማህበሩ ዋና መሥሪያ ቤት በሚገኝበት ቦታ
ሥልጣን ላለው ፍርድ ቤት ማመልከት ይችላል።
፮/ በዚህ አንቀጽ መሰረት ሥራዎችን ለማከናወን
የተደረገውን አስፇላጊ ወጪ ሁለ መሸፇን አለበት።