Article text
፫፻፶፫
354 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፩/ የታወቁ የማህበሩ ገንዘብ ጠያቂዎች ጥያቄያቸውን
ለሑሳብ አጣሪዎች ያላቀረቡ ከሆነ ሉከፇላቸው
የሚገባው ገንዘብ መጠን በፍርድ ቤት
ሉቀመጥላቸው ይገባል።
፪/ ለገንዘብ ጠያቂዎች ተመጣጣኝ ዋስትና
ካልተገባላቸው ወይም ከማህበሩ የሚጠየቁ
ግዳታዎች እስከሚፇጸሙ ድረስ የሀብት ክፍፍለ
ካልተላለፇ በስተቀር፤ የመፇጸሚያ ጊዜያቸው
ያልደረስ ወይም አከራካሪ የሆኑ ከማህበሩ የሚጠየቁ
ግዳታዎችን ለመፇጸም የሚያስችል ተመጣጣኝ
ገንዘብ በፍርድ ቤት መቀመጥ ይኖርበታል።