Article text
፶
51 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፩/ በልላ ሕግ በንግድ መዝገብ እንደሚገቡ የተደነገጉት
ላልች ሰዎች ወይም ድርጅቶች መመዝገባቸው
እንደተጠበቀ ሆኖ በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ የንግድ
ሥራ የሚሰራ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወይም
የውጭ አገር ዜጋ ወይም የንግድ ማህበር መመዝገብ
አለበት።
፪/ የዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፩) ድንጋጌ በተለይ
በሚከተለት ሰዎች ላይ ይፇጸማል፡ሀ) በዚህ ሕግ በአንቀጽ ፭ መሰረት ነጋዳ በሆነ
በማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወይም የውጭ አገር
ሰው፤
ለ) በዚህ ሕግ በአንቀጽ ፱ በተመለከተው የንግድ
ማህበር፤
ሐ) በማናቸውም የንግድ ሥራ በሚሰሩ የውጭ
አገር የንግድ ድርጅቶችና በማናቸውም
የውጭ አገር መንግሥት የንግድ እንደራሴዎችና
ወኪልች ወይም የመንግሥት ማህበራት ወይም
ድርጅቶች ላይ።
፶፩
52 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፫/ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፪)
(ሐ) በተመለከቱት
ድርጅቶች ላይ ተፇጻሚ የሚሆን ልዩ ሕግ
ይወጣል።