Article text
፩/ በንግድ መደብሩ የመያዣ ዋስትና ያላቸው ገንዘብ
ጠያቂዎች እና በዚህ ሕግ አንቀጽ ፩፻፵፩ ንዐስ
አንቀጽ
(፩) የተመለከቱት መቃወሚያ ያቀረቡት
ገንዘብ ጠያቂዎች የንግድ መደብሩ የሽያጭ ዋጋ
ለሚፇልጉት ክፍያ የማይበቃ የሆነ እንደሆነ
ገንዘብ ጠያቂዎቹ የንግድ መደብሩ በሐራጅ
እንዱሸጥ ፍርድ ቤቱን መጠየቅ ይችላለ።
፪/ ፍርድ ቤቱም የንግድ መደብሩ በውለ
በተመለከተው ዋጋ ላይ አንድ አስረኛው
ተጨምሮበት በሐራጅ እንዱሸጥ ያዝዛል።
፫/ በሐራጅ አብልጦ የሚገዛ ሦስተኛ ወገን የሆነ
ገዥ ሳይቀርብ የቀረ እንደሆነ የንግድ መደብሩ
ከፍተኛ ዋጋ ለሰጠው ገንዘብ ጠያቂ በሐራጅ
ይሸጣል።
፹፯
88 ____________________________________________________ የንግድሕግ