Article text
፩/ እያንዲንደ የሑሳብ ዓመት ከተዘጋበት ቀን ጀምሮ
ባለት አራት ወራት ውስጥ ቢያንስ አንድ መደበኛ
ጠቅላላ ጉባዔ መደረግ አለበት።
፪/ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፩) የተወሰነው የአራት
ወራት ጊዜ በማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ ወይም
አግባብ ባለው የመንግስት አካል ውሳኔ እስከ ስድስት
ወራት ሉራዘም ይችላል።
፫/ ጉባዔው የሚጠራው ማህበሩ የዲይሬክተሮች ቦርድ
ካለው በቦርደ፣ ቦርደ ካልጠራ ወይም ማህበሩ
ቦርድ ከላለው በሥራ አስኪያጅ፣ እነዚህ ካልጠሩ
ማህበሩ ኦዱተር ካለው በኦዱተሩ ወይም ከማህበሩ
ዋና ገንዘብ ከግማሽ በላይ ባዋጡ ባለአክሲዮኖች
ነው።
፬/ ከማህበሩ ዋና ገንዘብ ቢያንስ አስር በመቶ ባዋጡ
ባለአክሲዮኖች ጥያቄ ከቀረበለት በዚህ አንቀፅ ንዐስ
አንቀጽ
(፫) የተጠቀሰው አግባብ ያለው አካል ጉባዔ
መጥራት አለበት።
፫፻፹
381 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፭/ በዚህ አንቀጽ ኃላፉነት የተሰጣቸው አካላት ጉባዔውን
ለመጥራት ካልቻለ ወይም ፇቃደኛ ካልሆኑ ወይም
በማንኛውም ባለአክሲዮን ጠያቂነት በቂ ምክንያት
ሲኖር ፍርድ ቤት ጠቅላላ ጉባዔውን የሚጠራና
የመወያያ አጀንዲ የሚያዘጋጅ ሰው ሉሾም ይችላል።