Article text
፩/ የንግድ መደብር ባለቤት የሆነ ማንኛውም ሰው
ንግደን ራሱ ባያካሂደውም እንኳን የንግድ
መደብሩን በውል መያዣ ሉያደርገው ይችላል።
፪/ ይህም የዋስትና መያዣ ውል በጽሐፍ ካልተደረገ
በተዋዋይ ወገኖች መካከል አይፀናም፤ የዋስትና
መያዣ ውለም አግባብ ባለው ሕግ መሰረት
ካልተዘገበ ሦስተኛ ወገኖችን መቃወሚያ ሉሆን
አይችልም።
፫/ ከውል የመነጨ የዋስትና መያዣ ምዝገባ ዝርዝሩ
በልዩ ሕግ ይወሰናል።