Article text
፩/ አንድ ኩባንያ የዕዲ ሰነድችን በማውጣት መበደር
የሚችለው የገንዘብ መጠን በጸደቀው የመጨረሻ
የሀብትና ዕዲ ሑሳብ መግለጫ ውስጥ ከተመለከተው
የተከፇለ የማህበሩ ዋና ገንዘብ ሉበልጥ አይችልም።
፪/ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፩) የተመለከተው
ቢኖርም:-
ሀ) የማህበሩ የማይንቀሳቀስ ንብረት ለዕዲ ሰነድች
መያዣ ተደርጎ የተሰጠ እንደሆነና የወጡትም
የዕዲ ሰነድች ዋጋ ከመያዣው ዋጋ 2/3 (ሁለት
ሦስተኛ) የማይበልጥ እንደሆነ፤ ወይም
ለ) ከተከፇለው የማህበሩ ዋና ገንዘብ በላይ የወጡት
የዕዲ ሰነድች በተመዘገቡ ዋስትናዎች ወይም
በመንግስት በወጡ የግምጃ ቤት ሰነድች ወይም
መንግስት ዋስትና በገባላቸው ቦንድች ዋስትና
የተሰጠባቸው እና ከዋስትናነት ነፃ
የመውጫቸው ጊዜ ከዕዲ ሰነድች መክፇያ ጊዜ
የማይቀድም እንደሆነ ወይም መንግስት ወይም
፪፻፺፰
299 ____________________________________________________ የንግድሕግ
አንድ የመንግስት መሥሪያ ቤት በየዓመቱ
በሚከፍለው ገንዘብ ዋስትና የተገባላቸው
እንደሆነ፤ አንድ ማህበር በሀብትና ዕዲ ሑሳብ
መግለጫዎች ከተመለከተው የተከፇለ ዋና
ገንዘብ በላይ የተጻፇባቸው ዋጋ ያላቸው የዕዲ
ሰነድችን ለማውጣት ይችላል።
፫/ የዕዲ ሰነድች ዋጋ ተመልሶ ሙለ በሙለ እስኪከፇል
ድረስ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፪)
(ለ) መሰረት
በዋስትና የተሰጡት ሰነድች በባንክ ውስጥ መቀመጥ
አለባቸው፤ ለዕዲ ሰነድ ያዥ የሚከፇለውን ወለድ
እና ዋስትና የተገባላቸውን የዕዲ ሰነድች ዋጋ ጥቂት
በጥቂት ለመክፇል አስፇላጊ በሆነው መጠን ለእነዚህ
የዋስትና ሰነድች በየዓመቱ የሚከፇለው ገንዘብ
በባንክ በዝግ ሑሳብ መቀመጥ ይኖርበታል።
፬/ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፩) የተመለከተው ገደብ
የማይንቀሳቀስ ንብረት ለማፍራት በሚወሰድ ብድር
ወይም እርሻን መያዣ አድርገው በሚያበድሩ
ኩባያንዎች ላይ ተፇፃሚ አይሆንም።