Article text
፩/ የንግድ ተላላኪዎችና የንግድ እንደራሴዎች ውላቸው
ላልተወሰነ ጊዜ የሆነ እንደሆነና ነጋዳው ያለበቂ
ምክንያት ውለን በሰረዘ ጊዜ አግባብ ባለው ሕግ
መሰረት ካሣ የማግኘት መብት አላቸው።
፪/ ማናቸውም የንግድ ተላላኪዎች ወይም የንግድ
እንደራሴዎች አንዲች ጥፊት ሳያደርጉ ላልተወሰነ
ጊዜ ወይም ለተወሰነ ጊዜ የተዋዋለትን ውል
ነጋዳው የሰረዘው እንደሆነ ያመጧቸው ደንበኞች
ወይም ያስፊፈት ገበያ ወይም እነዚህን የመሳሰለ
የሰጧቸው ፍሬዎች ታስበው በርትዕ የሚገባ ካሣ
የማግኘት መብት አላቸው።