Article text
፩/ የሥራ አስኪያጁን ሥልጣን የአንድ የንግድ
ቅርንጫፍ ሥራን ለማስኬድ ብቻ የተወሰነ
ለማድረግ ይቻላል፤ ቢሆንም እንደዚህ ያለው
የሥልጣን መቀነስ ማስታወቂያ በንግድ መዝገብ
ካልገባ በዚህ ሕግ አንቀጽ ፩፻፫ እንደተመለከተው
በሦስተኛ ወገኖች ላይ መቃወሚያ ሉሆንባቸው
አይችልም።
፪/ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፩) ከተመለከተው
ውጪ ያለ ማናቸውም የሥልጣን መቀነስ በሦስተኛ
ወገኖች ላይ መቃወሚያ ሉሆንባቸው አይችልም።