Article text
፩/ የከሰረው ሰው ንብረት ጠባቂ ሥራውን እንደጀመረ
ባለዕዲው ያለትን መብቶች ለመጠበቅ አስፇላጊውን
እርምጃ መውሰድ አለበት፤
፪/ ባለዕዲው መልሶ በማደራጀት ወይም የንግድ ሥራው
በሚፇርስበት ወቅት ያላስመዘገበውን በማይንቀሳቀስ
ንብረት ላይ ያለውን የዋስትና መብት እና ላልች
የዋስትና መብቶች የከሰረው ሰው ንብረት ጠባቂ
ማስመዝገብ አለበት፤ የከሰረው ሰው ንብረት ጠባቂ
ንብረት ጠባቂ መሆኑን አስረድቶ በማይንቀሳቀስ
ንብረት ላይ ያለው ዋስትና የሚያስመዘግበው
በከሰረው ሰው ንብረት ስም ነው።