Article text
፩/ ጠቅላላ የመጠቀሚያ ጊዜያቸውን የጨረሱ ንብረቶችን
ከማህበሩ ሀብትነት ለመሰረዝ እንዱቻል ለንብረቶቹ
መተኪያ ገንዘብ በየዓመቱ መቀመጥ ይኖርበታል፤
በየዓመቱ ታስቦ ተቀማጭ የሚሆነው የመተኪያ
ገንዘብ መጠን የማይበቃ ሆኖ የተገኘ እንደሆነ
ከዕቃው እርጅና ጋር ተመጣጣኝ እንዱሆን መጠኑ
ከፍ ማለት ይኖርበታል።
፫፻፲፭
316 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፪/ ትርፍ ባይኖርም እንኳ በእያንዲንደ የሑሳብ ዓመት
ማለቂያ የማህበሩ ንብረቶች መተኪያ ገንዘብ እና
የእርጅና ቅናሽ ሑሳብ ተቀናሽ መሆን ይኖርበታል።
፫/ የማህበሩን ዋና ገንዘብ ለመሰብሰብ እና ለመጨመር
የተደረጉ ወጪዎች ወጪ ከተደረጉበት ቀን አንስቶ
እጅግ ቢዘገይ በአምስተኛው የሑሳብ ዓመት ማለቂያ
መተካት ይኖርባቸዋል።