Article text
፩/ በኪሣራ ምክንያት የማህበሩ ዋና ገንዘብ በአንቀጽ ፪፻፵፯ ንዐስ አንቀጽ
(፩) ከተመለከተው አነስተኛ
መጠን በታች ከሆነ የቀነሰው የዋና ገንዘቡ መቀነስ
በዚህ ሕግ አንቀጽ ፬፻፷፫ በተደነገገው መሰረት
በንግድ መዝገብ ከተመዘገበበት ቀን አንስቶ ባለው
አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ዋና ገንዘቡ ወደ አነስተኛ
መጠን ማደግ ይኖርበታል።
፪/ በዚህ ሕግ በአንቀጽ ፬፻፷፯ ሥር የተመለከተው
የገንዘብ ጠያቂዎች መብት አይነካም።
፫/ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፩) በተመለከተው
መሰረት ዋና ገንዘቡ ካልተስተካከለ ወይም ማህበሩ
ወደ ላላ ዓይነት ማህበር እንዱለወጥ ካልተደረገ
፫፻፵፩
342 ____________________________________________________ የንግድሕግ
በስተቀር ማንኛውም ጥቅም ያለው ወገን ማህበሩ
እንዱፇርስ ለፍርድ ቤት ማመልከት ይችላል።