Article text
በዚህ ሕግ አንቀጽ ፪፻፵፭ የተደነገገው ቢኖርም፤
ማንኛውም ወሳኝ ድምፅ ያለው ባለአክሲዮን ከዚህ
በታች ከተመለከቱት አንደን ፇፅሞ ከተገኘ ተጠያቂ
ይሆናል፦
፩/ የማህበሩን፣ የባለአክሲዮኖችን ወይም የማህበሩን
ገንዘብ ጠያቂዎችን ጥቅም ጉዲት ላይ የሚጥል
ሕገ-ወጥ ድርጊት ሆን ብል መፇፀም፤
፩፻፺፭
196 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፪/ የማህበሩን ንብረት ከባለአክሲዮኑ ንብረት ጋር
መቀላቀል፤
፫/ የማህበሩን እና የባለአክሲዮኑን ማንነት አለመነጣጠል
፣ ማህበሩን ለግል ወይም ለሶስተኛ ወገን ዓላማና
ጥቅም እንደ ሽፊን መጠቀም፤
፬/ ስለማህበሩ የፊይናንስ አቋም የማህበሩ ገንዘብ
ጠያቂዎችን ሉያሳስት የሚችል መረጃ ሆን ብል
ማውጣት፤
፭/ ከገበያ ዋጋ ባነሰ ክፍያ ወይም አግባብ ካለው የማህበሩ
አመራር ውሳኔ እና እውቅና ውጪ የማህበሩን ሀብት
ለራሱ ወይም ለሦስተኛ ወገኖች የግል ጥቅም ማዋል፤
ወይም
፮/ በሕግ ከሚፇቀደው በላይ የትርፍ ክፍያ መፇፀም።