Article text
፩/ የባለዕዲውን መክሰር የፇረደው ፍርድ ቤት
መክሰሩን ለማስታወቅ በሚሰጠው ፍርድ እሽግ
እንዱደረግ ለማዘዝ ይችላል። እሽጉም የሚደረገው
በመጋዘኖቹ፣ በሳጥኖቹ፣ በመዝገቦቹ፣ በሰነድቹ፣
በወረቀቶቹና እንደ አግባብነቱ የባለዕዲው በሆኑት
የቤት ዕቃዎች እና የሚንቀሳቀሱ ንብረቶች ላይ
ነው።
፪/ ነገር ግን ባለዕዲው የጠፊ ወይም ንብረቱን የደበቀ
ወይም ንብረቶቹን ያለአግባብ የተጠቀመ እንደሆነ
የሚመለከታቸው የመንግስት ባለሥል ጣን አካላት
በፇቃዲቸው ወይም በአንድ ገንዘብ ጠያቂ
አመልካችነት የመክሰር ፍርድ ከመሰጠቱ በፉት
በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፩) በተዘረዘሩት
ዕቃዎች ላይ እሽግን ለማድረግ ይችላለ።