Article text
፩/ አክሲዮን አይከፊፇልም።
፩፻፸፪
173 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፪/ ከአንድ በላይ የሆኑ ሰዎች የአክሲዮን የጋራ ባለቤት
በሆኑ ጊዜ የባለአክሲዮንነት መብታቸውን መጠቀም
የሚችለት የጋራ ወኪል በመሾም ነው።
፫/ የጋራ ወኪል ባልሾሙ ጊዜ ማህበሩ ለአንደ
የአክሲዮን የጋራ ባለቤት የሚሰጠው ማስታወቂያ
ወይም መግለጫ ለቀሪዎቹ የአክሲዮኑ የጋራ
ባለቤቶችም ጭምር እንደተሰጠ ይቆጠራል*
፬/ የአክሲዮን የጋራ ባለቤቶች ከባለአክሲዮንነት
ለሚመነጩ ኃላፉነቶች በአንድነትና በተናጠል
ተጠያቂ ናቸዉ።