Article text
፩/ የአንድ ማህበር የተጣራ ትርፍ የሚባለው የማህበሩ
ጠቅላላ ወጪዎች እንዱሁም የአላቂ ንብረቶች
መተኪያ ገንዘብና የእርጅና ቅናሽ ሑሳብ በሑሳብ
ዓመቱ ከተገኘው ጠቅላላ ገቢ ከተቀነሰ በኋላ
የሚገኘው ትርፍ ነው።
፫፻፲፯
318 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፪/ የሚከፊፇል ትርፍ ከሑሳብ ዓመቱ ትርፍ ላይ
የቀደምት ዓመታት ኪሣራዎች ከተቀነሱ በኋላ
በሑሳብ ዓመቱ ትርፍ ላይ በፉት ታስበው
ያልተከፊፇለ ትርፍችን እና ላልች ተጨማሪ
ገቢዎችን እና በልዩ ሁኔታ ጠቅላላ ጉባዔው
ከመጠባበቂያ ገንዘብ እንዱከፇል የፇቀደውን
ማንኛውንም ገንዘብ በመጨመር የሚገኝ ትርፍ
ነው።
፫/ የጠቅላላ ጉባዔው ውሳኔም ለትርፍ ተከፊይ
የሚሆኑት ገንዘቦች ከየትኛው የመጠባበቂያ ገንዘብ
ላይ እንደሚወሰደ ማመልከት ይኖርበታል።