Article text
፩/ የመክሰር ሥነ ሥርዓት እንዱከፇት በተሰጠው
ፍርድ የተነሳ በዕዲ የመውረሱ ሥራ የተቋረጠ
እንደሆነ የከሰረው ሰው ንብረት ጠባቂ የዕዲ ወራሽ
በሆነው ገንዘብ ጠያቂ ተተክቶ በዚህ ምዕራፍ
፮፻፴፩
632 ____________________________________________________ የንግድሕግ
ድንጋጌዎች መሰረት መያዣ የሆነውን ንብረት
ይሸጣል። የማይንቀሳቀሱ ንብረቶቹን የመሸጡ ሂደት
የመክሰር ሥነ ሥርዓት ተቆጣጣሪ ዲኛው ትዕዛዝ
በሰጠ በስምንት ቀናት ውስጥ ይጀምራል።
፪/ የማይንቀሳቀሰው ንብረት በግል ቢሸጥ ከሐራጅ ጋር
ሲነጻጸር ዋጋው የመጨመር ዕድል ያለው ከሆነ
የከሰረው ሰው ንብረት ጠባቂ የማይንቀሳቀሰውን
ንብረት በግል እንዱሸጥ ተቆጣጣሪ ዲኛው ሉፇቅድ
ይችላል።
፫/ የከሰረው ሰው ንብረት ጠባቂ የመክሰር ሥነ
ሥርዓት እንዱከፇት የተሰጠው ፍርድ ከተሰጠበት
ቀን አንስቶ በስድስት ወራት ውስጥ የሽያጩን
ሂደት ያልጀመረ እንደሆነ የከሰረው ሰው ንብረት
ጠባቂ በሚጠይቀው መሰረት ፍርድ ቤቱ በበቂ
ምክንያት የጊዜ ማራዘሚያ ካልሰጠ በስተቀር
ዋስትና ያለው ገንዘብ ጠያቂ በዕዲ የመውረስ
ሥልጣኑ ይመለስለታል። ከሽያጩ የሚገኘው ገንዘብ
በዚህ ምዕራፍ ድንጋጌዎች መሰረት ይከፊፇላል።
፮፻፴፪
633 ____________________________________________________ የንግድሕግ