Article text
፩/ ምርመራ እንዱደረግበት ትዕዛዝ የደረሰው ማህበር
የዲይሬክተሮች ቦርድ፣ ካለ የተቆጣጣሪ ቦርድ፣ ሥራ
አስኪያጆች፣ የማህበሩ ፀሐፉ ወይም ላልች የሥራ
ኃላፉዎች እና እንደራሴዎች ኢንስፔክተሮች
የሚጠይቋቸውን መዛግብትና ሰነድች ማቅረብና
ለሚጠይቋቸው ጥያቄዎች የተሟላ መልስ መስጠት
አለባቸው።
፪/ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፩) የተጠቀሱት የማህበሩ
ኃላፉዎች ኢንስፔክተሮች ሥራቸውን በአግባቡ
እንዲያከናውኑ መሰናክል የሆኑ እንደሆነ ኢንስፔክተሮች
ለሾማቸው አካል ሪፖርት ያቀርባለ፤ ሪፖርቱ የቀረበለት
አካል አግባብነት ባለው ሕግ መሰረት የወንጀል ክስ
እንዱቀርብ ጉዲዩን ለሚመለከተው አካል ማሳወቅ
አለበት።
፫/ በዚህ አንቀፅ ንዐስ አንቀፅ
(፪) የተደነገገው እንደተጠበቀ
ሆኖ ሪፖርት የቀረበለት አካል ምርመራውን በማናቸውም
፪፻፶፬
255 ____________________________________________________ የንግድሕግ
ሁኔታ የማድረግ ሥልጣኑ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ዝርዝሩ
በልዩ ሕግ በሚወሰነው መሰረት አስተዲደራዊ እርምጃ
መውሰድ ይችላል።