Article text
፩/ የተቋቋመበትን ዓላማ ሲፇጽም ወይም ለመፇጸም
ሳይችል ሲቀር፤
፪/ የማህበሩ አባላት እንዱቀጥል ካልተስማሙ
በስተቀር የማህበሩ የቆይታ ጊዜ ሲጠናቀቅ፤
፩፻፰
109 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፫/ ማህበርተኞች የንግድ ማህበሩ እንዱፇርስ
ሲስማሙ፤
፬/ በማህበሩ አባላት መካከል ተቃራኒ ስምምነት
ቢኖርም እንኳን በማህበሩ አባላት ጥያቄ ፍርድ
ቤት በበቂ ምክንያት ማህበሩ እንዱፇርስ ሲወስን፤
ወይም
፭/ የማህበሩ መክሰር በፍርድ ቤት ሲወሰን።
፮/ ለዚህ አንቀፅ ንዐስ አንቀፅ
(፬) ዓላማ በቂ
ምክንያት ማለት በማህበሩ አባላት መካከል ብርቱ
አለመግባባት ኖሮ አለመግባባቱ የማህበሩ ዓላማ
ከግብ እንዲይደረስ የሚያስተጓጉል ሲሆን ነው።
፯/ በዚህ አንቀፅ ንዐስ አንቀፅ
(፮) ላይ የተደነገገው
ቢኖርም የተወሰኑትን የማህበሩ አባላት
ድርሻቸውን ይዘው ከማህበሩ እንዱወጡ በማድረግ
በቀሪ አባላት ማህበሩ ዓላማውን ለማሳካት
በሚችልበት ሁኔታ ማስቀጠል የሚቻል በሆነ ጊዜ
አለመግባባቱ ማህበሩን ለማፍረስ እንደ በቂ
ምክንያት ተደርጎ አይወሰድም።
፩፻፱
110 ____________________________________________________ የንግድሕግ