Article text
፩/ የንግድ መደብር ሽያጭን የሚመለከቱ የዚህ
ምዕራፍ ድንጋጌዎች፡ሀ) በንግድ መደብር ላይ በሚደረግ ማናቸውም
ዓይነት ሽያጭ ወይም ማስተላለፍ፤ ላላ ነገር
በማስመሰል የተደረገም ቢሆን፤
ለ) የጋራ ባለሀብቶቹ ባቀረቡት ጥያቄ በሚደረግ
የሐራጅ ሽያጭ፤
ሐ) ካሣን ጨምሮ በሚደረግ ማናቸውም ክፍፍል፤
እንዱሁም ሽያጩ ወይም የመብት ማስተላለፈ
ወይም ክፍፍለ የንግድ መደብሩን ወይም
መልካም ስሙን የሚመለከት ሲሆን፤ ወይም
ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቱን ወይም ወኪል ጽሕፇት
ቤቱን የሚመለከት ሆኖ ነገር ግን ዋናውን
የንግድ መደብር ወይም የቅርንጫፍ መሥሪያ
ቤቱን ወይም የወኪል ጽሕፇት ቤቱን
፸፭
76 ____________________________________________________ የንግድሕግ
መልካም ስም ሳይጨምር በሚደረግ ሽያጭ
ወይም ማስተላለፍ ወይም ክፍፍል፤ ላይ
ተፇጻሚ ይሆናል።
፪/ የዚህ ምዕራፍ ድንጋጌዎች ሽያጩ የንግድ
መደብርን ወይም የንግድ መደብር መልካም ስምን
የሚመለከት ካልሆነ ወይም በማድበስበስ ወይም
በመደበቅ ይህን የሚያደርግ ካልሆነ በስተቀር
የንግድ መደብርን የተለያዩ አካላት ነጣጥል
በሚደረግ ሽያጭ ላይ ተፇፃሚ አይሆኑም።