Article text
፮፻፲፪
613 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፩/ በዚህ ክፍል መሰረት ንብረትን ለማስመለስ
የሚጠይቁ ሰዎች የመክሰር ሥነ ሥርዓት በተከፇተ
በሦስት ወር ውስጥ በአደራ ደብዲቤ ወይም ተቀባዩ
ለመቀበለ ማረጋገጫ ሉሰጥበት በሚችል ላላ
ማንኛውም ኤላክትሮኒክ መንገድ ለከሰረው ሰው
ንብረት ጠባቂ ንብረታቸውን ለማስመለስ ማመልከት
አለባቸው።
፪/ የከሰረው ሰው ንብረት ጠባቂ ማመልከቻው በደረሰው
በአንድ ወር ውስጥ በአደራ ደብዲቤ ወይም ተቀባዩ
ለመቀበለ ማረጋገጫ ሉሰጥበት በሚችል ላላ
ማንኛውም ኤላክትሮኒክ መንገድ ውሳኔውን
የሰጠበትን ምክንያቶች ለአመልካቹ በመግለጽ
ማመልከቻውን ሉቀበል ወይም ውድቅ ሉያደርግ
ይችላል።
፫/ የከሰረው ሰው ንብረት ጠባቂ ማመልከቻው በደረሰው
በአንድ ወር ውስጥ መልስ ያልሰጠ እንደሆነ
ማመልከቻው ተቀባይነት እንዲገኘ ይቆጠራል።
፬/ የከሰረው ሰው ንብረት ጠባቂ ማመልከቻውን
አልቀበልም ያለ እንደሆነ ማመልከቻውን ያቀረበው
የንብረቱ ወይም የመብቱ ባለቤት የከሰረው ሰው
ንብረት ጠባቂ ማመልከቻውን ውድቅ በማድረግ
፮፻፲፫
614 ____________________________________________________ የንግድሕግ
በሰጠው ውሳኔ ላይ ውሳኔው በደረሰው በአንድ ወር
ውስጥ ለተቆጣጣሪ ዲኛው ተቃውሞ ሉያቀርብ
ይችላል።
፭/ ተቆጣጣሪ ዲኛውም ማመልከቻው በደረሰው በአስራ
አራት ቀናት ውስጥ በማመልከቻው ላይ ውሳኔ
ይሰጣል።
፮/ እንደአግባቡ ማመልከቻውን ያቀረበው ሰው ወይም
የከሰረው ሰው ንብረት ጠባቂ ተቆጣጣሪ ዲኛው
በሰጠው ውሳኔ ላይ ውሳኔው በተሰጠ በአስር ቀናት
ውስጥ ለፍርድ ቤት ይግባኝ ማቅረብ ይችላለ።
፯/ ንብረት ለማስመለስ የቀረበው ማመልከቻ ተቀባይነት
ካገኘ የከሰረው ሰው ንብረት ጠባቂ ሥነ ሥርዓቱ
ከተከፇተ በኋላ ከንዐስ ተቀባዩ የተገኙ ማናቸውንም
ክፍያዎች ጨምሮ መብቱን፣ ዕቃውን ወይም
ንብረቱን ወዱያውኑ ይመልሳል።