Article text
፩/ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፫) ውስጥ
የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ በመጠባበቂያ
ጊዜው ወቅት የባለዕዲው ንብረት እና ጉዲይ
በባለዕዲው ይዞታ ውስጥ ይቆያለ።
፪/ መልሶ የማደራጀት ኃላፉው ወይም ተቆጣጣሪ ዲኛው
አስቀድመው እንዱፇቅደለት ሳያስፇልገው ባለዕዲው
የንግድ ሥራውን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች
በሙለ የማከናወን መብት አለው።
፫/ መልሶ የማደራጀት ሥነ ሥርዓት ከተከፇተ በኋላ
የስጦታ ውልች እና ዋስትና እና የንብረት የዋስትና
መብቶችን ጨምሮ ነገር ግን በዚያ ሳይወሰን
ከባለዕዲው መደበኛ የሥራ ሂደት ውጭ የሆኑ
ስምምነቶች ወይም ግብይቶች በሙለ በመልሶ
ማደራጀት ኃላፉው አስቀድመው መፇቀድ
አለባቸው።
፭፻፲፪
513 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፬/ መልሶ የማደራጀት ኃላፉው እና ተቆጣጣሪ ዲኛው
በማንኛውም ጊዜ የባለዕዲውን የሑሳብ መዛግብት
ሉመረምሩ ይችላለ።
፭/ መልሶ የማደራጀት ኃላፉው ሆነ ብል ገንዘብ
ጠያቂዎችን ያለመግለጽን ጨምሮ በዚህ አንቀጽ
ንዐስ አንቀጽ
(፫) ላይ የሚፇጸሙ ማናቸውንም
ጥሰቶች እንዱሁም ማንኛውንም የማጭበርበር
ድርጊት ለሚመለከታቸው የዐቃቤ ሕግ እና ሕግ
አስከባሪ አካላት ማሳወቅ ይኖርበታል።