Article text
፩/ ባለ አንድ አባል ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበርን
ለማቋቋም አባለ የሚሰጠው መግለጫ ሰነድችን
ለማረጋገጥ ሥልጣን በተሰጠው አካል ፉት መደረግ
አለበት፤ መግለጫውም በንግድ መዝገብ ውስጥ
መግባት አለበት።
፪/ መግለጫው የሚከተለትን ነገሮች ማሳየት አለበት ፦
ሀ) ማህበሩ አንድ አባል ብቻ ያለው መሆኑን፤
ለ) የአባለን ስም፤ዜግነትና አድራሻ፤
ሐ) አባለ የሞተ፣ የጠፊ ወይም በፍርድ የተከለከለ
እንደሆነ ስለ ወራሾቹ ወይም ስለአባለ ሆኖ
ሕጋዊ ተግባራትን እንዱፇጽም የታጨው
የንብረት ጠባቂ ሰው ስም፤
መ) ዕጩ ንብረት ጠባቂው ፍቃደኛ ሆኖ ኃላፉነቱን
የተቀበለ መሆኑን፤
ሰ) የማህበሩን ስም፤ዋና መሥሪያ ቤት፤ ካለትም
ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶቹን፤
፫፻፹፱
390 ____________________________________________________ የንግድሕግ
ረ) የማህበሩን የንግድ ዓላማ፤
ሰ) የማህበሩ ዋና ገንዘብ መጠንና፤ይኼው በሙለ
የተከፇለ መሆኑን የሚያሳይ መግለጫ፤
ሸ) በዓይነት የተከፇለ መዋጮ ካለ ግምቱን፤
ቀ) የሥራ አስኪያጁን ስምና ሥልጣን፤
በ) ካለ ኦዱተሩን፤
ተ) ማህበሩ የሚቆይበትን ጊዜ፤
ቸ) ማህበሩ የሥራ አፇጻጸም ሪፖርት
የሚያስታውቅበትን መንገድና ጊዜ፤
ኘ) ላልች በሕግ ወይም በአባለ እንዱካተቱ
የተወሰኑ ጉዲዮችን።