Article text
፩/ ለዚህ ምዕራፍ ዓላማ “ቁጥጥር” አለ የሚባለው እናት
ኩባንያው ብቻውን ወይም ከላልች ባለኣክሲዮኖች
ጋር በመሆን የተቀጥላ ኩባንያውን የፊይናንስ እና
፬፻፪
403 ____________________________________________________ የንግድሕግ
የአሰራር ፖሉሲዎችን የመንደፍ እና የመምራት
ሥልጣን ሲኖረው ነው።
፪/ የዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፩) አጠቃላይ አነጋገር
እንደተጠበቀ ሆኖ፤አንድ እናት ኩባንያ የአንድን
ተቀጥላ ኩባንያ ከግማሽ በላይ ካፒታል የሚወክለ
ድምፅ የመስጠት መብት የሚያጎናጽፈ አክሲዮኖችን
በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በባለቤትነት ከያዘ
በተቀጥላው ላይ ቁጥጥር እንዲለው ይወሰዲል፤
ሆኖም፤ እናት ኩባንያው በተቀጥላው ውስጥ
በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የያዘው ይህ መጠን
ያለው ድርሻ በልዩ ሁኔታ ቁጥጥር እንደማይሰጠው
በግልጽ ማሳየት ከተቻለ የ« ቁጥጥር » መኖር ሕጋዊ
ውጤቶች አይኖሩም።
፫/ አንድ ኩባንያ በልላ ኩባንያ ውስጥ ያለው ድምፅ
የመስጠት መብት የሚያጎናጽፍ የአክሲዮን ድርሻ
የሁለተኛውን ኩባንያ ዋና ገንዘብ ግማሽ ወይም
ከዚያም ያነሰ የሚወክል ቢሆን እንኳን ከዚህ በታች
ከተዘረዘሩት ሁኔታዎች አንደ ወይም ከዚያ በላይ
ተሟልቶ ሲገኝ በሁለተኛው ላይ ቁጥጥር እንዲለው
ይቆጠራል፦
፬፻፫
404 ____________________________________________________ የንግድሕግ
ሀ) ከላልች ባለአክሲዮኖች ጋር በተደረገ
ስምምነት ከግማሽ በላይ የሆነውን ድምፅ
የመስጠት መብት ከተጎናጸፇ፤
ለ) በመመስረቻ ጽሁፍ ወይም በልላ ስምምነት
የኩባንያውን የፊይናንስ እና አሰራር
ፖሉሲዎችን የመቆጣጠር መብት ከተጎናጸፇ፤
ሐ) የኩባንያውን ንግድ የመምራት ሥልጣን ካለው
የኩባንያው ከፍተኛ የአስተዲደር አካል አባላት
መካከል አብዛኛዎቹን የመሾምና የመሻር
መብት ካለው፤ ወይም
መ) የጠቅላላ ጉባዔ ወይም ተመሳሳይ ሥልጣን
ያለው የኩባንያው ውሳኔ ሰጪ አካል ውስጥ
አብላጫ ድምፅን መስጠት ወይም ማግኘት
በመቻለ በተጨባጭ የኩባንያውን ንግድ
መቆጣጠር ሲችል።
፬/ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ ፫
(ሐ) እና
(መ) መሰረት ቁጥጥር አለ የሚባለው የኩባንያውን
ግማሽ ወይም ከግማሽ የሚያንሱ አክሲዮኖች የያዘው
፬፻፬
405 ____________________________________________________ የንግድሕግ
ኩባንያ አንድን ኩባንያ የመምራት ሥልጣን ካለው
የኩባንያው ከፍተኛ የአስተዲደር አካል ወይም ውሳኔ
ሰጪ አካል አባላት ውስጥ አብዛኛዎቹን ለሁለት
ተከታታይ የፊይናንስ ዓመታት መሾም የቻለ
እንደሆነ ነው፤ በፊይናንስ ዓመቱ ውስጥ ይሄው
ኩባንያ በሁለተኛው ኩባንያ ውስጥ ያለው ድምፅ
የመስጠት መብት ከጠቅላላው አርባ በመቶ በላይ
ሲሆን እና በዚሁ በሁለተኛው ኩባንያ ውስጥ
በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከእርሱ የበለጠ የድምፅ
ድርሻ ያለው ላላ ባለአክስዮን ከላለ የሁለተኛውን
ኩባንያ ከፍተኛ ሥራ አስፇጻሚ ወይም ውሳኔ ሰጪ
አካል አባላት እርሱ ስለመሾሙ ግምት
ይወሰድበታል።