Article text
፩/ አንድ ሰው በራሱ ወይም በወኪለ አማካይኝት
በነጋዳነት ለመመዝገብ ማመልከቻ ካላቀረበ
በስተቀር በነጋዳነት ሉመዘገብ አይችልም።
፪/ ነጋዳው የንግድ ሥራውን ከመጀመሩ በፉት
ማመልከቻውን ማቅረብና መመዝገብ አለበት።
፫/ ማመልከቻው በዚህ ሕግ በአንቀጽ ፸፱ ንዐስ አንቀጽ
(፪) በተደነገገው መሰረት መዝጋቢው አካል
በሚያስተዲደረውና በሚቆጣጠረው ድረ-ገጽ ላይ
በመረጃ መረብ አማካይነት ላቀርብ ይችላል።