Article text
፩/ የማህበሩ ገንዘብ ጠያቂዎች የማህበሩን መለወጥ
የተቀበለ መሆናቸው ካልተረጋገጠ በስተቀር፤
ኃላፉነታቸዉ ያልተወሰነ ሸሪኮች የመለወጡ ውሳኔ
በንግድ መዝገብ ከመመዝገቡ በፉት ማህበሩ ለገባው
ግዳታ ከነበረባቸዉ ኃላፉነት ነፃ አይሆኑም።
፪/ የአክሲዮን ማህበር፣ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር
ወይም ባለ አንድ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር
ወደ ሽርክና ማህበር የተለወጠ እንደሆነ ሸሪኮቹ
ከለውጡ በፉት ማህበሩ ለገባበት ዕዲ በግል ተጠያቂ
አይሆኑም።
፫/ የማህበሩ ገንዘብ ጠያቂዎች ስለማህበሩ መለወጥ
ማህበሩ ያሳለፇው ውሳኔ በተመዘገበ ደብዲቤ ወይም
ቀድመው በመረጡት የኤላክትሮኒክ ዘዳ
ተልኮላቸው ከተላከበት ቀን አንስቶ ባለት ሰላሳ
ቀናት ውስጥ ለውጡን እንደሚቃወሙ በግልጽ
በጽሁፍ ካላሳወቁ የማህበሩን መለወጥ እንደተቀበለ
ይቆጠራል።
፬፻
401 ____________________________________________________ የንግድሕግ