Article text
፩/ የንግድ መደብሩን ወደ ላላ ስፍራ ለማዛወር
የሚፇልግ ባለዕዲ የንግድ መደብሩን የዋስትና
መያዣ አድርገው ለያዙት ገንዘብ ጠያቂዎች
ማስታወቅ አለበት፤ሆኖም ገንዘብ ጠያቂዎች
መዛወሩን እንዱያውቁ ያልተደረገ እንደሆነ ወይም
እንዱያውቁት ከተደረገው የማዛወሪያ ቀን ቢያንስ
ከአንድ ወር በፉት አስቀድሞ ዝውውሩ ከተፇፀመ
ገንዘብ ጠያቂዎቹ ዕዲቸው እንዱከፇል ወዱያውኑ
መጠየቅ ይችላለ።
፪/ የንግድ መደብሩን በዋስትና የያዙ ገንዘብ
ጠያቂዎች በቦታው መዛወር ምክንያት የመደብሩ
፺፫
94 ____________________________________________________ የንግድሕግ
ዋጋ ይቀንሳል ብለው ከገመቱ በዚህ ሕግ አንቀጽ ፩፻፶ የተሰጣቸውን መብት መጠቀም ይችላለ።
፫/ ገንዘብ ጠያቂዎች በንግድ መደብሩ መዛወር
ከተስማሙና የንግድ መደብሩ የተዛወረው
በተመዘገበበት ክልል ውስጥ የሆነ እንደሆነ
ዝውውሩን መሰረት አድርጎ ምዝገባው
እንዱስተካከል መጠየቅ አለባቸው፤ የንግድ
መደብሩ ቀድሞ ከተመዘገበበት ክልል ውጭ
የተዛወረ እንደሆነ ገንዘብ ጠያቂዎቹ የተዛወረው
የንግድ መደብር አዱሱ ዋና መሥሪያ ቤቱ
በሚገኝበት ክልል የዋስትና መያዣው እንደ አዱስ
መመዝገቡን ማረጋገጥ አለባቸው።
፬/ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፫) መሰረት
ምዝገባው የተስተካከለ ወይም አዱስ ምዝገባ
የተከናወነ እንደሆነ ማስተካከያው ወይም አዱሱ
ምዝገባ የመጀመሪያው ምዝገባ ከተከናወነበት ጊዜ
ጀምሮ የፀና ይሆናል።