Article text
፩/ አንድ ሸሪክ ድርሻውን ማህበርተኞች ዘንድ
ተቀባይነት ላገኘ ላላ ማህበርተኛ ወይም ሦስተኛ
ወገን ሳያስተላልፍ በሞት፣ በሕመም፣በኪሣራ
ወይም በልላ ማናቸውም ምክንያት ከማህበሩ የወጣ
እንደሆነ በእርሱ እግር ተተክቶ ድርሻውን የመጠየቅ
መብት ላለው ሰው ድርሻው ተሰልቶ በገንዘብ
ይሰጠዋል፣ በሞተው ወይም በወጣው ሰው ምትክ
በማህበሩ አባል የመሆን ጥያቄ ተቀባይነት የለውም።
፪/ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፩) መሰረት የድርሻ
ዋጋ ሲሰላ የወጣው ሸሪክ ማህበሩ ውስጥ የነበረው
፩፻፵፪
143 ____________________________________________________ የንግድሕግ
ገቢ የተደረገ መዋጮ፤ የማህበሩ ዕዲዎች ከተከፇለ
በኋላ ከሚቀረው ተራፉ ሀብት ወይም የተጠራቀመ
ትርፍ ውስጥ እርሱ የነበረው ድርሻ እና በወጣበት
ወቅት በመሰራት ላይ የነበሩ ሥራዎች የሚያስገኙት
ትርፍ ግምት ውስጥ መግባት አለበት።