Article text
፩/ በዚህ ሕግ አንቀጽ ፭፻፺፫ ውስጥ የተመለከተው
ቢኖርም የማይንቀሳቀስ ንብረት የንግድ ኪራይ
ውልች የቀጠለ እንደሆነ ጊዜው ከማለቁ በፉት
ወዱያውኑ ኪራይ እንዱከፇል የሚደነግጉ
ማናቸውም የውል ድንጋጌዎች መልሶ በማደራጀት
ሥነ ሥርዓት ወቅት ለመጠባበቂያ ጊዜው
የመጀመሪያ አራት ወራት ወይም በመክሰር ሥነ
ሥርዓት ወቅት በአንቀጽ ፯፻፵፬ ውስጥ በተደነገገው
መሰረት የንግድ ሥራው ለሚቀጥልበት ጊዜ ያህል
ተፇጻሚ አይሆኑም።
፬፻፶፬
455 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፪/ የማይንቀሳቀስ ንብረት የንግድ ኪራይ ውልች
የቀጠለ እንደሆነ እና አከራዩ የኪራይ ውለ
በተፇረመበት ወቅት አጠቃላይ የኪራይ ክፍያዎችን
የተቀበለ እንደሆነ ወይም እንዱህ ላለው ክፍያ በቂ
ዋስትናዎችን ያገኘ ከሆነ አከራዩ ሥነ ሥርዓቱ
ከተከፇተ በኋላ የሚፇጠሩ ማናቸውንም ወቅታዊ
እና የወደፉት የኪራይ ክፍያዎች መጠየቅ
አይችልም።
፫/ ማናቸውም የውል ድንጋጌዎች ቢኖሩም የከሰረው
ሰው ንብረት ጠባቂ የኪራይ ስምምነቶችን ለተቀረው
ጊዜ ያህል ሉያስተላልፍ ይችላል፤ ሆኖም የንግድ
ቦታው የሚሰጠው አገልግልት ሉቀየር አይችልም፤
አግባብ በሚሆንበት ጊዜ ተቆጣጣሪ ዲኛው
አገልግልቱ እንዱቀየር ሉፇቅድ ይችላል።