Article text
፩/ አክሲዮን በባለአክሲዮኑ ስም በመመዝገብ ይወጣል።
፪/ ተቃራኒ ስምምነት ቢኖርም እንኳን ይህ ሕግ
ከመውጣቱ በፉት ላምጪው የሚለ አክሲዮኖች
በሚገኙባቸው ማህበሮች ለአምጪው በሚል የወጡ
አክሲዮኖች ባለቤት የሆነ ማንኛውም ሰው
አክሲዮኖቹ በስም በሚመዘገብ እንዱለወጡለት
ማህበሩ ዘንድ በመቅረብ ይህ አዋጅ በነጋሪት ጋዜጣ
ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሦስት ዓመት ውስጥ
ማመልከት አለበት።
፫/ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፪) መሰረት
የአክሲዮን ዓይነት ለመለወጥ የሚያስፇልገውን
ወጪ የሚሸፍነው የአክሲዮን ዓይነት እንዱቀየርለት
ጥያቄ ያቀረበው ባለአክሲዮን ነው።
፬/ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፪) ሥር የተመለከተው
የሦስት ዓመት የሽግግር ጊዜ ካለፇ በኋላ ላምጪው
በሚል የወጡ አክሲዮኖች የአባልነት መብት
አያሰጡም።