Article text
፩/ ቅርንጫፍ ማለት ለአንድ የውጭ የግል ድርጅት፣
የንግድ ማህበር ወይም ላላ ተመሳሳይ ድርጅት
ጥቅም በኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ በመሳተፍ ትርፍ
ለማግኘት በተደራጀ ሁኔታ የሚሰራ ቋሚ አካል
ነው፤ ቅርንጫፍ የሚደራጀው ለተወሰነ ወይም
ላልተወሰነ ጊዜ ሉሆን ይችላል።
፪/ ቅርንጫፍ ከዋናው የግል ድርጅት፣ የንግድ ማህበር
ወይም ላላ ተመሳሳይ ድርጅት የተለየ የሕግ
ሰውነት የለውም።
፬፻፴፭
436 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፫/ ከቅርንጫፍ እንቅስቃሴ የሚመነጩ ግዳታዎችም
ሆነ መብቶች የዋናው የግል ድርጅት፣ የንግድ
ማህበር ወይም የላላ ተመሳሳይ ድርጅት መብት
እና ኃላፉነት (ፓትሪሞኒ) አካል ይሆናለ።