Article text
፩/ ኦዱተሮች በዲይሬክተሮች ቦርድ ለማህበሩ ጠቅላላ
ጉባዔ በቀረበ ሪፖርት ላይ ያላቸውን አስተያየት
የሚገልጽ ሪፖርት በጽሁፍ ለጠቅላላ ጉባዔ ማቅረብ
አለባቸው፤ የሚያቀርቡት ሪፖርት ኦዱተሮቹ
ሥራቸውን እንዳት እንዲከናወኑ ማሳየት
ይኖርበታል።
፪/ ኦዱተሮች በዲይሬክተሮች ቦርድ የቀረበውን የሑሳብ
ሪፖርት ጠቅላላ ጉባዔው እንዱያፀድቀው ወይም
ውድቅ እንዱያደርገው ሀሳብ ማቅረብ አለባቸው።
ኦዱተሮች ስለትርፍ አከፊፇል ዲይሬክተሮቹ
፪፻፵፮
247 ____________________________________________________ የንግድሕግ
ባቀረቡት ሀሳብ ላይ ለጠቅላላ ጉባዔው
አስተያየታቸውን መስጠት አለባቸው።
፫/ ጠቅላላ ጉባዔው በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፩) የተጠቀሰው ሪፖርት ካልቀረበለት በስተቀር በሑሳብ
ሚዛን መግለጫው ላይ መነጋገር የለበትም።