Article text
፩/ አንድ ሸሪክ ድርሻውን ለላላ ማህበርተኛ ወይም
ለሦስተኛ ወገን ሳያስተላልፍ ከማህበሩ ከወጣ እና
ማህበሩ ሥራውን ከቀጠለ በማህበርተኞቹ
ስምምነት መሰረት የሚወሰን ክፍያ ይሰጠዋል።
፪/ ስለዚህ ጉዲይ ስምምነት የላለ እንደሆነ በማህበሩ
ውስጥ የነበረው ገቢ የተደረገ መዋጮ፤ የማህበሩ
ዕዲዎች ከተከፇለ በኋላ ከሚቀረው ተራፉ ሀብት
ወይም የተጠራቀመ ትርፍ የራሱን ድርሻ እና
በወጣበት ወቅት በመሰራት ላይ የነበሩ ሥራዎች
የሚያስገኙት ትርፍ ግምት ውስጥ ያስገባ መጠን
ታስቦ በገንዘብ ይከፇለዋል።