Article text
የማግኘት መብታቸው ላይ ክርክር የተነሳበት ገንዘብ
ጠያቂዎች
፩/ ማንኛውም ገንዘብ ጠያቂ የንብረት ዋስትና ወይም
ቅድሚያ የማግኘት መብት ያለው ከሆነ እና
የንብረት ዋስትናው ወይም ቅድሚያ የማግኘት
መብቱ ላይ ክርክር የተነሳ ከሆነ ገንዘብ ጠያቂው
ዋስትና እንደላለው ገንዘብ ጠያቂ በሥነ ሥርዓቱ
ላይ ሉሳተፍ ይችላል።
፪/ በንብረት ዋስትና ወይም ቅድሚያ በማግኘት መብት
ላይ የሚነሳ ማንኛውም ክርክር በፍርድ ቤቱ ውሳኔ
ይሰጥበታል።