Article text
፩/ የባለዕዲው ዋና የጥቅም ማዕከል የሚገኘው ኢትዮጵያ
ውስጥ ከሆነ ዋናውን ሥነ ሥርዓት ለመክፇት
ሥልጣን ያላቸው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ናቸው፤
፬፻፷፪
463 ____________________________________________________ የንግድሕግ
ዋና የጥቅም ማዕከል ማለት መደበኛ በሆነ መልኩ
ባለዕዲው ጥቅሙን የሚያስተዲድርበት ስፍራ ሲሆን
ይኸውም በሦስተኛ ወገኖች መረጋገጥ መቻል
አለበት፤ ኩባንያን ወይም በሕግ የሰውነት መብት
የተሰጠው ሰውን በተመለከተ ተቃራኒ ማስረጃ
እስከላለ ድረስ የተመዘገበ ቢሮው የሚገኝበት ቦታ
ዋና የጥቅም ማዕከል ተደርጎ ይቆጠራል፤ የተፇጥሮ
ሰውን በተመለከተ ተቃራኒ ማስረጃ እስከላለ ድረስ
ዋና የሥራ ቦታው ዋና የጥቅም ማዕከል ተደርጎ
ይቆጠራል።
፪/ ዋና የጥቅም ማዕከለ ኢትዮጵያ የሆነ ባለዕዲን
በተመለከተ ለቅድመ ጥንቃቄ ዕዲን መልሶ የማዋቀር
ሥነ ሥርዓት፣ መልሶ የማደራጀት ሥነ ሥርዓት
እና የመክሰር ሥነ ሥርዓት እንዱከፇት የሚሰጥ
ፍርድ ዓለም አቀፊዊ ተፇጻሚነት አለው።
፫/ የባለዕዲው ማንኛውም የሥራ ቦታ ኢትዮጵያ ውስጥ
የሚገኝ ከሆነ የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች በሀገር
ውስጥ ያለ ንብረቶችን የሚመለከት ሥነ ሥርዓት
ለመክፇት ሥልጣን አላቸው፤ የሥራ ቦታው
፬፻፷፫
464 ____________________________________________________ የንግድሕግ
ባለዕዲው ሰውን እና ንብረቶችን ተጠቅሞ ጊዜያዊ
ያልሆነ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የሚያደርግበት የሥራ
ቦታ ነው።
፬/ ኢትዮጵያ ውስጥ የሥራ ቦታ ያለውን ባለዕዲ
የሚመለከት በሀገር ውስጥ ያለ ንብረቶችን
የሚመለከት ሥነ ሥርዓት ተፇጻሚነቱ በኢትዮጵያ
ድንበር ውስጥ በሚገኙ የባለዕዲው ንብረቶች
የተወሰነ ነው።
፭/ የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች በዚህ ሕግ አንቀጽ ፮፻
ንዐስ አንቀጽ
(፪) ውስጥ በተመለከተው መሰረት
እንዱህ ካለው ሥነ ሥርዓት በቀጥታ የሚመነጩ
እና ከእርሱ ጋር የቅርብ ትስስር ያላቸውን ክሶች
የማየት ሥልጣን አላቸው።