Article text
፫፻፷፬
365 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፩/ ባለአክሲዮን በዓይነት መዋጮ የከፇለ እንደሆነ
የመመስረቻ ጽሁፈ የመዋጮውን ዓይነትና ዋጋ፣
ላልች ባለአክሲዮኖች የተቀበለበትን ዋጋ እና
ከማህበሩ ዋና ገንዘብ ውስጥ በዓይነት ለከፇለው
ባለአክሲዮን የተሰጠውን የአክሲዮን ድርሻ መጠን
ማሳየት አለበት።
፪/ የዓይነት መዋጮ የሚገመትበት መንገድ
በባለአክሲዮኖች ይወሰናል።
፫/ በዓይነት የተከፇለ መዋጮ በተከፇለበት ጊዜ
ለተደረገው ግምት ትክክለኛነት ባለአክሲዮኖቹ ሁለ
ለሦስተኛ ወገኖች በአንድነትና በተናጠል ኃላፉዎች
ይሆናለ።
፬/ በዓይነት የተከፇለ መዋጮ ግምት ከዋጋው በላይ
ሆኖ ከተገኘ በዓይነት ያዋጣው ባለአክሲዮን
በግምቱና በትክክለኛ ዋጋ መካከል ያለውን ልዩነት
በጥሬ ገንዘብ መክፇል አለበት፤ ከዋጋው በላይ
ስለመገመቱ ባያውቁም እንኳን ባለአክሲዮኖች ለዚህ
ገንዘብ መከፇል በአንድነትና በተናጠል ኃላፉዎች
ይሆናለ።
፭/ የማህበሩ ሥራ አስኪያጅ እና ማህበሩ የዲይሬክተሮች
ቦርድ ካለው ቦርደ በዓይነት የተዋጣው ንብረት
እንደነገሩ ሁኔታ በማህበሩ ስም መመዝገቡን እና
፫፻፷፭
366 ____________________________________________________ የንግድሕግ
አስፇላጊው የንብረት ባለቤትነት ማስረጃ በማህበሩ
ስም መዘጋጀቱን ማረጋገጥ አለባቸው።