Article text
፩/ በዚህ ሕግ አንቀጽ ፬፻፰ መሰረት የተሰጡ
ውሳኔዎች ጉባዔ በተደረገ በአስራ አምስት ቀናት
ውስጥ በማህበሩ ወይም በዕዲ ሰነድ ያዦች ቡድን
ወኪልች ወይም እነርሱ በላለ ጊዜ በማንኛውም
የዕዲ ሰነድ ያዥ ለፍርድ ቤት ቀርበው መጽደቅ
ይኖርባቸዋል፤ ውሳኔዎቹ በፍርድ ቤት ካልጸደቁ
ተፇጻሚነት አይኖራቸውም።
፪/ ውሳኔዎቹን የተቃወሙ ወይም በጉባዔው ያልተገኙ
የዕዲ ሰነድ ያዦች ውሳኔው እንዲይጸድቅ መቃወም
ይችላለ።