Article text
፩/ ባለዕዲው መልሶ በማደራጀት ኃላፉ ቁጥጥር ሥር
ሆኖ መልሶ የማደራጀት ሥነ ሥርዓት በተከፇተ
በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ ሁለንም ንብረቶቹን
የያዘ የንብረት ዝርዝር ያዘጋጃል፤ ዝርዝሩ በተለይ
የሚከተለትን ያካትታል፡ሀ) የክፍያ ጥያቄያቸውን መጠን፣ ስማቸውን እና
አድራሻቸውን የሚገልጽ የገንዘብ ጠያቂዎች
ዝርዝር፤
፭፻፲፱
520 ____________________________________________________ የንግድሕግ
ለ) ባለሀብትነታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ የተፇጸሙ
የሽያጭ ውልችን ጨምሮ በሂደት ላይ ያለ
ውልች፤
ሐ) በማስያዣነት ይዞታቸው የተላለፇ ንብረቶችን፣
በንግድ ሥራው ላይ የተሰጡ መያዣዎችን እና
የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን ጨምሮ የግል
ዋስትናዎች እና ለዕዲ ማስያዣነት የዋለ
ንብረቶች፤
መ) ባለዕዲው አንደኛው ተካራካሪ ወገን የሆነባቸው
በሂደት ላይ ያለ የሕግ ሥነ ሥርዓቶች፤
ሰ) በጉምሩክ ሥር ያለ እና በመጋዘን የተቀመጡ
ዕቃዎች፤
ረ) በኪራይ ቤቶች ውስጥ የሚገኙ ተንቃሳቃሽ
ዕቃዎች፤
ሰ) ታክሶች፣ ቀረጦች እና የማህበራዊ ዋስትና
ክፍያዎች።
፪/ የንብረት ዝርዝሩ በሁለት ቅጂዎች ተዘጋጅቶ
አንደኛው ለፍርድ ቤቱ መዝገብ ቤት ሹም ገቢ
፭፻፳
521 ____________________________________________________ የንግድሕግ
የሚደረግ ሲሆን ላላኛው ደግሞ መልሶ የማደራጀት
ኃላፉው ዘንድ ይቀመጣል።