Article text
በዚህ ሕግ ከአንቀጽ ፮፻፸፩ እስከ ፮፻፸፯ በተደነገገው
መሰረት የመክሰር ፍርድ ከመሰጠቱ አስቀድሞ
አጠራጣሪ በሆነ ጊዜ ውስጥ በባለዕዲው የተሰሩት
ሥራዎች መልሶ በማደራጀት ሥነ ሥርዓት ማዕቀፍ
ውስጥ መልሶ በማደራጀት ኃላፉው ፇራሽ ያልተደረጉ
እንደሆነ የከሰረው ሰው ንብረት ጠባቂ ሥራዎቹ ፇራሽ
እንዱደረጉ ለማድረግ እርምጃዎችን ይወስዲል፤ ሥራዎቹን
ፇራሽ ለማድረግ ዓላማ የከሰረው ሰው ንብረት ጠባቂ
መልሶ የማደራጀት ኃላፉው ሥልጣን ይኖረዋል።