Article text
፩/ በመዝገብ ማስገባት የሚቻለው ለመመዝገብ
የሚያመለክተው ሰው በጽሁፍ መግለጫውን
ባቀረበ ጊዜ ነው።
፪/ በመዝገብ የማስግባቱ ተግባርም ሆነ የጽሁፍ
መግለጫው ለንግድ ምዝገባ ዓላማ ተብል በተለየ
ሁኔታ የተዘጋጀና መዝጋቢው አካል
በሚያስተዲደረው ድረ-ገጽ በመረጃ መረብ
አማካኝነትም ሉከናወን ይችላል።
፫/ ከመዝገቡ ውስጥ የሚሰረዝ ነገር ሲኖር በዚህ ሕግ
በአንቀጽ ፺፮ በተመለከተው ባለሥልጣን ሲታዘዝ
ሉሰረዝ ይችላል።