Article text
፩/ መልሶ በማደራጀት ወይም በመክሰር ሥነ ሥርዓት
ውስጥ በንግድ ሥራ እንቅስቃሴ ላይ ያለ ድርጅት
በመንቀሳቀስ ላይ እንዲለ ያልተሸጠ እንደሆነ
የከሰረው ሰው ንብረት ጠባቂ ግዙፊዊ ህልዎት
ያላቸው እና የላላቸው ንብረቶቹን ጨምሮ የንግድ
ሥራውን ሀብቶች ይሸጣል።
፪/ የከሰረው ሰው ንብረት ጠባቂ በሐራጅ ወይም በግል
ሽያጭ የመሸጫ ዋጋውን ይበልጥ ከፍ የማድረግ
ዕድል ባለው በአንደኛው መንገድ የንግድ ሥራውን
ሀብቶች ለመሸጥ ሉወስን ይችላል፤ የሽያጩን
መንገድ በተቆጣጣሪ ዲኛው ያስጸድቃል።