Article text
፩/ ከንግድ መደብር ሽያጭ ዋጋ ላይ የዋስትና መያዣ
ያላቸው ገንዘብ ጠያቂዎች የቀዲሚነት መብት
አሎቸው።
፪/ የዋስትና መያዣ ያላቸው ገንዘብ ጠያቂዎች
የቀደምትነት ደረጃ በተመዘገቡበት ቀን ቅደም
ተከተል መሰረት ይወሰናል። ሆኖም የዋስትና
መያዣቸውን በአንድ ቀን ውስጥ ያስመዘገቡ
ገንዘብ ጠያቂዎች እኩል ደረጃ ይኖራቸዋል።
፫/ ሻጩ በንግድ መደብሩ ላይ ያለው ከሕግ የመነጨ
የዋስትና መያዣ ከውል ከመነጨ የዋስትና
መያዣ ቅድሚያ ይኖረዋል።