Article text
፩/ የአንድ ማህበር ዲይሬክተር ከሚመራው ማህበር ጋር
በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ የጥቅም
ግጭት ሉፇጥሩ ከሚችለ ሁኔታዎች ራሱን ማራቅ
አለበት።
፪/ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፩) የተመለከተው
ክልከላ ማህበሩ ሉጠቀምባቸው ቢችልም ባይችልም
በተለይ ንብረትን፣ መረጃን እና የንግድ ዕድልን
መጠቀም በተመለከተም ተፇጻሚ ይሆናል።
፫/ አንድ የዲይሬክተሮች ቦርድ አባል የነበረ ሰው
ከኃላፉነት ከተነሳ በኋላም ቢሆን የቦርድ አባል
በነበረበት ወቅት በሥራው ምክንያት ያወቀውን
፪፻፳፪
223 ____________________________________________________ የንግድሕግ
መረጃ እና የንግድ ዕድል ለራሱም ሆነ ለሦስተኛ
ወገን ጥቅም ማዋል አይችልም።
፬/ በዚህ አንቀጽ የተደነገገው ክልከላ ዲይሬክተሩ
ከማህበሩ ጋር ከሚያደርገው የሥራ ውል ጋር
በተያያዘ ሉነሳ የሚችል የጥቅም ግጭትን
አይመለከትም።
፭/ አግባብነት ባለው የዚህ ሕግ ድንጋጌ መሰረት
የዲይሬክተሮች ቦርድ ወይም የማህበሩ ጠቅላላ
ጉባዔ በዚህ አንቀጽ የተጣለውን ክልከላ በማንሳት
ፇቃድ ሉሰጥ ይችላል።