Article text
፩/ አክሲዮን በመያዣ ወይም በአላባ የተሰጠ እንደሆነ
ተቃራኒ ስምምነት ከላለ በስተቀር በማህበሩ
ጉባዔዎች ድምፅ የመስጠት መብት የሚኖረው
አክሲዮኑን በመያዣ የያዘው ወይም የአላባ ጥቅም
ያለው ሰው ነው።
፪/ አክሲዮኑ አዱስ አክሲዮኖችን ለመግዛት የቀዲሚነት
መብት የሚሰጥ ከሆነ ይህ የቀዲሚነት መብት
የባለአክሲዮኑ ሆኖ ይቀጥላል።
፩፻፸፫
174 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፫/ በመያዣ ለተሰጠ አክሲዮን የሚከፇል ቀሪ ገንዘብ
በማህበሩ በተጠየቀ ጊዜ ገንዘቡን መክፇል ያለበት
ባለአክሲዮኑ ነው፤ ባለአክሲዮኑ የተባለውን ገንዘብ
ሳይከፍል የቀረ እንደሆነ ማህበሩ አክሲዮኑን
በአንቀጽ ፪፻፹፱ መሰረት መሸጥ ይችላል።
፬/ ለአክሲዮኑ የሚከፇል ቀሪ ገንዘብ በማህበሩ
በተጠየቀ ጊዜ አክሲዮን በአላባ የተሰጠው ሰው
መክፇል አለበት፤ ሆኖም የአላባው ጊዜ ሲጠናቀቅ
የከፇለው ገንዘብ እንዱመለስለት የመጠየቅ መብት
አለው።
፭/ ድምፅ የመስጠት መብት የሚሰጡ አክሲዮኖችን
በመያዣ ወይም በአላባ የያዙ ሰዎች በማህበሩ
መመዝገብ አለባቸው፤ ማህበሩ ከመዘገበ በኋላ
የምዝገባ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት መስጠት
አለበት።